የትግሬ ወያኔ ወደ እውነተኛ ቁመናው ሲመለስ!

የግለስብ ሁለንተናዊ ቁመናው የሚገለጥ ከሚመጣበት መህበረሰብ አኳያ ነው። ግለስቦቹ ተቧድነው የሚፈጥሩትም ማህበርና ድርጂትም ላይ የዚያው ማህበረሰብ አሻራ አብሯቸው ይኖራል። ለምሳሌ በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ማህበረሰቦችን በዚህ አኳያ መዳሰስ ይቻላል። ይህን ማህበራዊ እይታ ያፍሪካ ቀንድ ወስጥ የሰፈሩ የተለያዩ ማህበረሰቦች የሚጋሩት ቢሆንም በሱማሌ፣ በኤርትራና በትግሬ ማህበረሰቦች መሀል ባያሌው የሚታየው በቤተሰባዊ (ክላን) አመለካከት ዙሪያ የሚታይ ማህበረሰባዊ መከፋፈል የላቀ ነው።

በዚህ ረገድ ዛሬ ለነጻዪቱ ሱማሌ መበታትን ከፍተኛውን ሚና የተጫወተ የህዝቧ በክላን ዙሪያ ያጠነጠነ አመለካከት በማደግ ላይ የነበረውን ሀገራዊ አመለካከት ስለደፈጠጠው ነው። ዚያድ ባሬ የኦክቶበር አብዮት ብሎ የሰየመውን የ1962ዓም የመፈንቅ ለመንግስት ሲመሰርት ዋና የአገዛዙ መመሪያ አድርጎ ያስቀመጠው የሱማሊያን አምስት የተለያዩ ግዛቶችን በአንድ የተጠቃለለች ታላቅ ሱማሌ ስር የማምጣትን ህልም ነበር። ዚያድ ባሬ ይህንን መመሪያ ዋናው የአገዛዙ ርእዮት ሲያደርግ ኢላማው የማህበረሰቡ ዋና ድክመት የሆነውን የቤተሰባዊ(የክላን) አመለካከትን በአንድ ሱማሊያ ተብላ በምትጠራ አዲስ ሀገር ዙሪያ ለማሰለፍ ነበር። እንዳለውም ፊደል ላልነበረው ቋንቋ የላቲን ፊደልን እንዲይዝ አደረገ። የሀገሪቱን የአስተዳደር አይነት ሶሻሊዝም ነው ብሎ አወጀ። ሀገራዊ ታላቅነቱን እውን የሚያደርግለት ጦሩን ገነባ።

ከፍተኛ የሆነ ብሄረተኝነትን የሚቀሰቅስና በአንድ የጋራ ጠላት ዙሪያ የሚያስቆም ጠላት ተመረጠለት። ኢትዮጵያ ዋና የጋራ የተለያዩትን አስተባባሪ የምትሆን ተደርጋ የሱማሌ ብሄራዊ ጠላት ሁና ተመረጠች። የዚያድ ባሬ የማህበረሰብ ችግርን በጋራ ሰው ሰራሽ ጠላት ዙሪያ እንዲቆም የማድረግ አባዜ በጸሓይ እንደተመታ ጤዛ የረገፈው በኢትዮጳያ ላይ በወሰደው ወራራ ላይ ሆነ። ሱማሌ በወረራው በደረሰባት ሽንፈት ወደነበረችበት ቁመናዋ እንድትሸበሸብ ተደረገች። የህብረተሰቧ ቁመና በአሸዋ ላይ ከተገነባው የታላቋ ሱማሌ፣ ከሰው ሰራሽነት ወደእውነቱ የክላን ዓለም ስሪቷ እንድትመለስ ሆነ። መሀሉ ዳር ሆነ። ሁሉም ወደጎጆው ተመልሶ ከፍርስራሹ የቻለውን ለማንሳት የራሱን ጦር አቁሞ ይፋለም ገባ ። እናም ሱማሌ ፈረሰች።

ይህ ክስተት ባጋጣሚ የመጣ ሳይሆን መሆን የነበረበት ነው የሆነ፡፡ የኤርትራንም አፈጣጠር በትይዩ ማስቀመጥ ይቻላል። የኤርትራን አንድ ሀገርነት እውን ለማድረግ እንደ ዲናሚት ፈንድቶ እንዳልነበር ሊያደርግ የሚችለውን የአውራጃ ፖለቲካን አርግቦ አዲስ ሀገር ለመመስረት የተደረገው ትግል የአዲሲቱ ሀገር ዋና መገለጫ ታሪክ ነው ማለት ይቻላል። እንደ ሱማሊያው የክላን ታሪክ ሁሉ የኤርትራውን የአውራጃ ፖለቲካን ለማዳፈንና አንድ አመለካከት ለመፍጠር የተሄደበት መንገድ አንድ የጋራ ጠላት ኢትዮጵያን መፍጠር አስፈላጊ ነበር። በዚህ ጎዳና ውስጥ ሲጓዙ ደም ያራጨ የርስ በርስ ጦርነቶችንም አስተናግደዋል። ከኤርትራ እንደሀገር መቆም በኋላም ባለው የሸአብያ አገዛዝ ስር እንደገና ተመልሶ ያቆጠቆጠና ለእንደገና መፍረሷ ምክንያት ስለመሆኑ የሚነገርለት የአውራጃዊ ፖለቲካ ነው። ይህ በሚገባ በፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድሀኔ “ኤርትራ እንደናት ሀገር፣ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም”” በሚል በ2013 የቀረበ ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ በሚገባ የተነገረ ጉዳይ ነው፡፡

ሙሉውን ለ ማንበብ ይህን ጫኑ

About Our Store

ZTech Computers Services offers computer support for small to medium size business in Auckland area. We travel to your workplace or office and troubleshoot a wide range of IT problems on site. We also offer residential IT support and we fix computer of all types. Our online store offers various types of services including second-hand books, computer accessories, laptop, desktop computers at a reasonable price.

Contact Us

64 210731462
zenebetsega@msn.com
info@ztechltd.co.nz

Twitter

Facebook