ከመነሻው ወያኔ አንግቦት የተነሳበት ዓላማው የተሳሳተ፣ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ዐማራ መሆኑ ግልጽ ነው። ይህም የተሳሳተ ዓላማ በተለያዩ ወቅቶች ፣ዓላማውን ያልደገፉ ቡድኖች ባነሷቸው ጥያቄዎች የመከፋፈል እና የመፈራረስ አደጋዎች በከፍተኛ ደረጃ እየጋረጡበት እንደ እባብ ሞቶ አፈር እየላሰ ከዚህ የደረሰ መሆኑ ይታወቃል። የትግሬ-ወያኔን ለመበታተንና ለማፍረስ የሚችሉ ነባራዊ ሁኔታዎች ተሟልተው እያለ፣ ገፍቶ የሚጥል ጠናካራ አገራዊ ዕራይ ያነገበ ድርጅት አለመኖር፣ላለፉት 43 ዓመታት አገርና ትውልድ የሚያጠፋ ሥራ እንዲሠራ ሠፊ ዕድል አገኘ። በራሱ ውስጥ የተፈጠሩትን ችግሮች በመጠቀም ገፍቶ መጣል ባለመሞከሩ፣ ወያኔ ድክመቶቹን የጥንካሬውና የመታደሻው መገለጫዎች እያደረገ ሕዝብን ለማተለል ተጠቀመበት። የ1969 እና 1970 ዎቹ «የሕንፍሽ ሕንፍሽ» የትግራይ አውራጃዎች ልዩነት እንቅስቃሴ፣ የድርጅቱን መሥራቾችና መሪዎች የነበሩት አረጋዊ በርሃና ግደይ ደብረጽዮን ከድርጅቱ የማባረር ሂደት፣ በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ማግሥት በነተወልደና መለስ የተፈጠረው ክፍፍል የትግሬ-ወያኔ ወደ መቃብር አፋፍ ያደረሱት ክስተቶች ነበሩ። ለነዚህ ችግሮች ያበቁትም ጠንካራ ተቃዋሚ ኖሮና በርሱ ተገፍቶ ሳይሆን፣ ዓላማቸው ስሕተት በመሆኑ፤ኢትዮጵያዊነት በመንፈስ፣ ዐማራው በፀሎት፣ በትዕግሥትና ትዕግሥቱን እንደፍራት ሲቆጥሩት ደግሞ ከ2008 ዓም ጀምሮ በመጡበትና ሊገባቸው በሚችለው ቋንቋ ማነጋገር መጀመር ለሌላ ዙር የትግሬ-ወያኔ ክፍፍልና መፈራረስ ሠፊ በር እንደከፈተ እያየን ነው።
በሌላ በኩል ካለፉት 3 ዓመታት ጀምሮ በመካከለኛው የአገሪቱ ክፍለ-ሀገሮች፣ አውራጃዎችና ወረዳዎች የተቀጣጠለው የኦሮሞ ወጣቶችየተቃውሞ እንቅስቃሴ ተከታታይነት፣ ከዐማራው የጎበዝ አለቆች እንቅስቃሴ ጋር ጎን ለጎን መፋፋም፤ «ከየትኛውም ጊዜ ከነበሩት አገዛዞች በበለጠ የሕዝቡን አንድነት አረጋግጫለሁ፣ ሰላም አስፍኛለሁ፣ ከፍተኛ የሆነና በያመቱ 11% ዕድገት አስመዝግቤአለሁ፤ዲሞክራሲያዊአሠራርና ባሕል እየገነባሁ ነው፣ የዚህም መሠረቱ ሕዝቡ ወዶ ያጸደቀው ሕገ-መንግሥት የአገዛዙ መመሪያ በመሆኑ ነው» እያለ፣ በሚለፍፍበት ጊዜ፣ ሕዝባዊ እንቢተኝነቱ በመላ አገሪቱ ዳር እስከ ዳር መቀጣጠል ያሳደረበት ከፍተኛ ጫና ፣የሰላምና የብልጽግናዬ መስተዋት ነው የሚለውን «ሕገ-መንግሥት» አግዶ ወታደራዊ አገዛዝ ለ10 ወሮች አስፍኖ ሕዝቡን በገፍና በግፍ መግደሉ፣ ማሰሩናማሰቃየቱ ይታወቃል።
ይህ ሕዝባዊ አመጽ በ2009ዓም ላይ በመላ አገሪቱ መስፋፋትና ፣ከሁሉም በላይ ፣«ዐማራው ላይነሳ አከርካሪውን መተነዋል»፤ «ዐማራና ኦሮሞን እሳትና ጭድ አድርገናቸዋል»፣በማለት ኢትዮጵያን እስከ ወዲያኛው በእኛ ፍልጎት ያሻንን እናደርጋታለን፣ ካልሆነም አፈራርሰናት ወደ ትግራይ-ትግሪኝ ግዛታችን እንገባለን ብለው በሚፏልሉበት ወቅት፣ እሳትና ጭድ እንዲሆኑና በአጥፊና ጠፊነት ጎራ እንዲሰለፉ ያደረጓቸው ዐማራና ኦሮሞ ነገዶች ሰምና ፈትል፣ውኃና ወተት በመሆን፣ ተነጥለው እንደቆዩ ላምና ጥጃ እምቧ እያሉ በናፍቆት መተቃቀፍ የወያኔን በሁለቱ ነገዶች ፍቺ ዕድሜ የማራዘም ሕልም ወደ ቀን ቅዠት እንደለወጠው እያስተዋልን ነው። ገድለን ቀብረነዋል ያሉት ዐማራ መቃብር ፈንቅሎ ፣ትፋሽ ስቦ፣ በከፍተኛ እልክ ማንነቱንና እርሱነቱ ለማሳየት በመጡበት መንገድ በመጓዝ፣ በሚገባቸው ቋንቋ ማነጋገር ሲጀምር፣ከሁሉም በላይ ኢሉባቡር ላይ የወያኔ ሰላዮች በደንጋይ ተወግረው መገደል ወያኔንና ተከታዩን ብርክ ከቶታል። ይህም የወያኔን አመራር ከሁለትና ከዚያም በላይ ሰንጥቆታል። «እናቴ ትግሬ ባልሆንሽ የሚባልበት ዘመን ይመጣል» የሚባለው በትግራይ ሕዝብ ዘንድ በፍርሓት የሚነገረው የቆየ ትንቢት መፈጸሚያው ወቅት ላይ ተደርሷል የሚሉት አባባሎች በስፋት በማኅበረሰቡ ውስጥ መነገር፣ የወያኔን ባለሥልጣን ነን ባዮች ብርክ ከቷል።
በዐማራውና በኦሮሞው ወጣቶች ከእልክና ከቁጭት የመነጨው የፀረ-ወያኔው እንቅስቃሴ፤ ከዓመት ዓመት ሥፋትና ጥንካሬ እያገኘ መጓዝ ያሰጋው የወያኔ ጥርቅም ፣ እንዳለፉት ሁሉ ይህን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለመግታት የተለያዩ እርምጃዎች የሞት ሙቱን ለመውሰድ በጥድፊያ ላይ ይገኛል። የሚወስዳቸው የአፈና እና የዕመቃ ዘግናኝ እርምጃዎች፣ እንዳለፉት ሁሉ የትግሬን የበላይነት ለማስጠበቅ እስከተቻለ ድረስ ማናቸውንም ዓይነት እርምጃ ከመውሰድ የማይመለስ መሆኑ ካለፉት ድርጊቶቹ መገንዘብ ከመቻሉም በላይ፣ ሕዝባዊ እንቅስቃሴው ያሳደረበት የፍርሃት ቆፈን ማየል እርምጃው ካለፉት የከፋ ጅምላ ጭፍጨፋ እንደሚሆን የተለያዩት መረጃዎች ያሳያሉ።