በካሊፎረኒያ ስቴት በሳን ሆዘ ከተማ በሃያት ሪጀንሲ ሳንታክላራ ሆቴል በሰኔ 26/2006 (July 3/2014) በሞረሽ ወገኔ የአማራ ሲቪክ ማሕበር በተዘጋጀው ሕዝባዊ ስብሰባ በአቶ ጌታቸው ረዳ የቀረበ ጥናታዊ ጽሑፍ። getachre@aol.com
የተከበራችሁ የመድረኩ አዘጋጆች እኔን ከእነዚህ የታወቁ ዓለም አቀፍ ምሁራን ጋር ሆኜ አገራችን በአሁኑ ሰዓት ስለ አለችበት ሁኔታ ለመነጋጋር ስለጋበዛችሁኝ፤ ምስጋናዬ የላቀ ነው። አመሰግናለሁ።
ከሁሉም አስቀድሜ አንድ ነጥብ ለማስረገጥ የምፈልገው ጉዳይ፤ በዚህ ስብሰባ በእንግድነት ስጋበዝ፤ የምሰነዝራቸው አስተያየቶች እና ትችቶች ማንም የፖለቲካ ቡድን ወይንም ድርጅት ወክዬ ሳይሆን እራሴን አንደ የኢትዮፕያን ሰማይ ድረግጽ አዘጋጅነቴ እንደ ጌታቸው ረዳ በግል የሚወክል ነው። ማንም ተቃዋሚ ወይንም ሚዲያ በምሰነዝረው አስተያየት የመከራከር የመተቸት መብቱ የተጠበቀ ነው። ከዚህ በታች የማቀርበው ጽሑፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በስፋት የልተመረመረ ታሪክ በኔ በትግራያዊ ነገድ በኢትዮጵያዊ ዜጋ ተደረገ የመጀመሪያ ጥናት ስለሆነ ፤ የታሪክ ምሁራን ለምርምር ሊጠቀሙበት ፈቅጃለሁ።